ቱሪዝም በአለም አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ የሆነ ፍች የለውም ለዝህ ምክንያቱም የቱሪዝም ትምህርት /discipline/ ገና በማደግ ላይ ያለ በመሆኑ ነው፡፡ ነገርግን በአብኣኛዎቹ ባለሙያዎችና የዓለም የቱሪዝም ድርጅት እንደሚለው ቱሪዝም ማለት ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው /አካባቢያቸው / ተነስተው ከአንድ አመት ላልበለጠና ከ24 ሰአት ላላነሰ ጊዜ ወደ ሌላ አካባቢ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሆኖ የረፍት ጊዜን ለማሳለፍ ፣ ለመዝናናት ፣ ለንግድ ስራ ወይም ለሌላ ተግባር የሚያደርጉት ጉዞ ቱሪዝም ይባላል፡፡
ነገርግን ሁሉም ተጓዦች ጎብኝዎች ሊባሉ አይችሉም ጎብኝዎች ለመባል የተለያዩ መስፈርቶች መሟላት አለባቸው ከእነዚህም መስፈርቶች
1.purposive criterion የጉብኝት አላማ ሲኖር
2.spatial criterion ጉብኝቱን የሚያደርገው ተጓዠከመኖሪያ አካባቢው ርቆ መሄድ እንዳለበትና ከቱሪስት ተቀባይ ወገን የተለያዩ አገልግሎቶች ሲያገኝ ፣
3.Temporal criterion የጉብኝት የጊዜ ገደብም መኖር ያለበት ሲሆን ከአንድ ምሽት ማነስ እንደለሌለበትና ከአንድ አመት መብለጥ እንደሌለበት የዓለም የቱሪዝም ድርጅት ያስቀምጣል፡፡
ከአንድ ምሽት ካነሰ ወይም ከአንድ አመት ከበለጠ ግን ቱሪስት ሳይሆኑ ሌላ ስያ ሊሸፃቻ ይችላለል፡፡
ጎብኚዎች የሚያደርጉት ጉዞ አንድን አላማ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ከሚከተሉት አላማ አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡
Leisure /Recreation/ Holiday ሰዎች አእምሯቸው በስራ ወይም በሌላ ምክንየያት ሲደክም ከመኖሪያ አከባያቸው ርቀው ወደሌላ አከባቢ በመሄድ አእምሮን ዘና የሚያደርጉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መስህብ ሃብት በማየት አእምሯቸው እንዲዝናና ለማድረግ የሚታቀድ ጉብኝት ነው፡፡
Business Travel የተለያዩ ስራዎች ለመስራት ከመኖሪያ ቦታው ወደ ቱሪስት ተቀባይ ቦታ የሚደረግ ጉዞ ነው፡፡ በዚህ የጉብኝት ዓይነት ቱሪስቱ ጉብኝት ለማድረግ የሚወስነው በቱሪስት ተቀባይ ቦታ ሄዶ በሚያከናውነው ተግባር /ስራ/ይሆናል፡፡
ቱሪስትም ለመባልለስራው ስራ የሚከፈለው አበል ከቱሪስት ተቀባ ድርጅት መሰረት ያደረገ ከሆነ ተጓዡ እንደ ቱሪስት አይቆጠርም ፡፡ መገንዘብ ያለብን ጎብኚዎች በቱሪስት ተቀባይ ቦታ የሚቆዩበት ጊዜ የተለያዩ አገልግለለቶችን ስለሚያገኙ ለአከባው ህብረተሰብ የተለያዩ ገቢ የሚያስገኙ የስራ እድሎችን ስለሚፈጥሩና ገንዘቡን በቱሪስት አማካኝነት ከቱሪስት አመንጪወደ ቱሪስት ተቀባይ ፈሰስ ይደረጋል፡፡
Visiting Friends and Relatives ጎብኚዎች መሰረት አድርገው የሚሄዱት ዘመድ ወዳጅ ወይም ጓደኛ ለመጠየቅ ሲሆን በአብዛኛው የዚህ መሰረት ተጓዦች በስራ ወይም በሌላ ምክንያት ከአከባቢያቸው እርቀው የሚሄዱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
Sport በአለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ከተሞች ከቱሪዝም ጋር በተያያዘ ተጠቃሚ እያደረገ ያለ ዘርፍ ነው፡፡ አትሌቶችና አሰልጣኘች የመሳሰሉት በዚህ ይካተታሉ ፡፡ በአብዛኛ ትልልቅ የሽር ጽታድድሮችን ለመመልከት የሚመጣ ህዝብ መሸረጹ የዚህ አይነት ጉብኝት ነው፡፡
Religion በዚህ ስር የሚካተቱት ሃማኖታዊ ጉዞዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣- የሃጂና ኡምራ ጉዞና ወደሮምና ኢየሩሳሌም የሚደረጉ ጉዞዎችን መጥቀስ ይቻላ፡፡
Health ከበሽታቸው ለማገገም የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ሰዎች ወደ ተለያዩ አከባቢዎች ይጓዛሉ፡፡ ለምሳሌ፣- እንደ ኩባ ያሉ ሃገሮች ብዙ ታካሚዎች ወደሃገራቸው እንዲመጡ ለማበረታት ለታካሚዎች የህክምና ወጭን ይቀንሳሉ፡፡ስለዚህ ታካሚዎች ወደ ተለያዩ ተቋማት በሚያደርጉት ጉዞ የአእምሮ እረፍት /ሰላም/ያገኛሉ፡፡
Education /study/ ከመኖሪያ ቤታቸው ርቀው የሚማሩ ወይም የሚማራመሩ ተማሪዎች ወይም ምሁሮች እንደ ቱሪስት ይቆጠራሉ፡፡ይህ የሚሆነው ግን ምንም ዓይነት ክፍያ ሳይከፈላቸውና ገቢ በሚያስገኝ ስራ ላይ ሳይሰማሩ ለትምህርት ወይም ለመመራመር ብቻ ከሄዱ ነው፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ተግባራት ውጭ ከመኖሪያ ቀያቸው ተነስተው ወደሌላ ቦታ የሚጓዙ ሁሉ ቱሪስቶች ሊባሉ አይችሉም ፡፡ ለምሳሌ፣- ጊዚያዊ/ቋሚ/ስደተኞች፤ ዲፕሎማቶች፤አምባሳደሮች፣የተለያዩ ሰላም አክባሪ ወይም ወራሪ ወታደሮች ፤ዘላኖች፤በደንበር አከባቢ የሚሰሩ ሰራተኞች የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡