Build Your Dream

የአለም ቱሪዝም ቀን World tourism day

This is the post excerpt.

 የአለም ቱሪዝም ቀን በየአመቱ መስከረም 17 በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን በአሉ እንዲከበር የተወስነው መስከረም 1979 እ.ኤ.አ በስፔን ሃገር ቶምሊንስ ከተማ በተካሄደው ሦስተኛ የአለም ቱሪዝም ድርጅት አጠቃላይ ስብሰባ ላይ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ክብረ በአል የተካሄደው እ.ኤ.አ በ1998 ዓ.ም ሲሆን በአስተባባሪነት በአሉን ያስተናገደችው ሃገር ሜክሲኮ ነበረች፡፡

የዘንድሮው የአለም ቱሪዝም ቀን በአለም ለ34ኛ ጊዜ በሃገራችን ለ28ኛ ጊዜ በክልላችን ለ24ኛ ጊዜ በዞናችን ለ18ኛ ጊዜ እና በከተማ አስተዳደራችን ደግሞ ለ10 ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ይውላል፡፡

የአለም ቱሪዝም ቀን የሚከበርበት ዋና አላማ ለአለም ማህበረሰብ ቱሪዝም ያለውን ባህላዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ግንዛቤን ለመፍጠር ነው፡፡

የቁንጅና ንግስት ያች ወሎየዋ፤

ሸጋ የሚያበቅለው ናፍቆኛል ቀየዋ፤

አፈሩን አድርገጎት የቆንጆ መብቀያ

ኮምበልቻ የዘሩት ያብባል ወልድያ

14409932_1785897285025249_6559179289959227941_o

 

ወልድያ 

 

ወልድያ ከተቆረቆረች ከ230 አመት በላይ የሚሆናት ሲሆን የተመሰረተችው የጁ እና ጎንደርን አጣምረው ያስተዳድሩ በነበሩት  በታላቁ ራስ አሊ ዘመን በ1777 ዓ.ም እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ያስረዳል::

የከተማዋ አመሰራረት ከብዙዎቹ የኢትዩጵያ ከተሞች ጋር ተመሳሳይ የሆነ ባህሪ ይጋራሉ፡፡ የጥንት ጊዜ ከተሞች  የሚመሰረቱት ከየአቅጣጫው የሚመጣ ጠላትን ለመቆጣጠር እና ለመመከት ከሚያስችል ቦታ ላይ ነበር፡፡

ይህ በመሆኑ  ምክኒያት ወልድያ ተራራን  ራስጌ አድርጋ እንድትቆረቆር ሆኗል፡፡ ከተማዋ ስያሜ ጋር በተያያዘ ደግሞ 2 አፈታሪኮች ይነገራሉ፡፡

20160830_075901

ከገብረኤል ተራራ ጀርባ የሚገኘው ማመጫ ተክለሀይማኖት ገዳም 2009.

የመጀመሪያው ራስ አሊ ቤተ መንግስታችውን ከሰሩበት ገብርኤል ተራራ ላይ ሆነው ቁልቁል ሲመለከቱ የቀድሞው አዋጅ መንገሪያ የዛሬው ማክሰኞ ገበያ ላይ ነጭ ነገር ይመለከታሉ፡፡ ንጉሱም አሽከራቸውን ስለ ነገሩ ምንነት አጣርቶ እንዲመለስ ይልኩታል፡፡

የተላከውም አሽከር በቦታው ሲደርስ የአራስ ጨርቅ ታጥቦ የተሰጣ  መሆኑን ሲነግራችው ነጉሱም ቀበል አድርገው “ወልዳ!” ብለው ሳያስረግጡ የአካባቢውን የአነጋገር ዘየ ተከትሎ ወልድያ የሚለው ስያሜዋ ሆኖ እንደቀረ ይነገራል፡፡

ሁለተኛው ከየአቅጣጫው የሚመጡ ነጋዴዎች የሚገናኙባት ከተማ የነበረች በመሆነኗ በኦሮሞኛ ወልድያ የሚል ስያሜ እንደተሰጣት ይነገራል፡፡

ሆኖም ወልድያ የሚለው ቃል  በኦሮመኛ መገናኛ ወይም በተራራ የተከበበች የሚለውን ትረጉም ይይዛል፡፡

ወልድያ እና መስህቦቿ

 

የቆንጆዎች መንሃሪያ ወልድያ ከተማ በተለያዩ የቱሪዝም ዘረፎች መስህብነቷ እየጎላ ፣ እያበበ ፣ እየተመነደገ ይገኛል፡፡ የወልድያ ከተማ  መስህብነቷ ጥንታዊና የተልያዩ የሀገራችን ከተሞች ማለትም አክሱም ፣ ጎንደር የአዲስ አበባ እና የላስታ ላሊበላ መተላለፊ ዋና መንገድ ከመሆነኗ የሚጀምር ሲሆን እንግዳ ተቀባይነቷ ፣ ማኅበረሰቡ ተቻችሎ የመኖር እሴቱ እና  ለኑሮ ምቹ የሆነው አየር ንብረቷ መስህቦቿ እንድለሙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

በዚህም ምክኒያት የዞን እና የጉባላፍቶ ወረዳ መቀመጫ እንድትሆን አስችሏታል፡፡

ይሁን እንጅ ከተማዋ 230 አመታትን ያስቆጠረች ቢሆንም በተለያዩ ምክኒያቶች የቱሪዝም ሀብቷ በወጉ ሳይለሙ የቆዩ ቢሆንም አሁን ግን  በወልድያ ባህልና ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት ያለሰለሰ ጥረት በዙሪያዋ የሚገኙ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ቅርሶቿ እንዲፈለጉ ፣ እንዲመዘገቡ እና የተጎዱትም ጥረገና እንድደረግላችው በማድረግ  ፣ በከተማዋ የሚገኝ የአገልግሎት ሰጭ ተቀቋማት ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ ፣ የአካባቢው ወግና ባህል ተጠብቆ እንዲኖር በማድረግ እና የተለያዩ ስራዎችን በመስራት እንዲሁም መስህቦቿን በማስተዋወቅ ለአካባቢው የቱሪዝም ልማት ፣ ለመሰርተ ልማት ግንባታ እና ለኢንቨስትመንት ፍሰት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡

ወልድያ ለኑሮም ለንግድም ምቹ ናት፡፡ በውስጧ ከ12 ያላንሱ ባንኮች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል የኢትጲያ ንግድ ባንካ(ፒያሳ ፣ አዳጎና ገጓንደር በር) ፣ ዳሽን ባንክ ፣ ንግድ ባንካ(ፒያሳ ፣ አዳጎና ገጓንደር በር) ፣ ዳሽን ባንክ ፣ አቢሲኔያ ባንክ ፣ ወጋገን ባንክ ፣ ህብረት ባንክ ወዘተ በአጠቃላይ በውስጧ ከ12 በላይ የተቀላጠፈ የባንክ አገልግሎት ባለቤት ናት፡፡

7af69804-4a8e-4f9a-8d83-ed3af7c17bb9

ወልድያ በለውጥ ጎዳና 2017 .

እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ ተቋማት ማለትም በትምህርት ፣ በመዝናኛ ፣ በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ፣ በቀላል እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም እያደገ በመጣው የኢንቨስትመንት እና የቱሪስት ፍሰቷ ወልድያ ለኑሮ ማራኪነቷ እንዲጨምር አድርጎታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአማራ ክልል ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ደረጃ ከተመረጡ የኢንዱስትሪ መንደሮች ውስጥ አንዷ ናት፡፡

ሳምንታዊ የማክሰኞ ገበያ ፣ የማመጫ ተክለሀይማኖት ገዳም ፣ የደብረ ሙዚየሞቿ ፣ የአካባቢው ባህል እና  የእደ ጥበብ ስራዎቿ ፣ አመታዊ የቃና ዘገሊላ ወልድያ ሚካኤል ፣ የጥምቀት ፣ የአረፋ እና የኢድ አል-ፈጥር ባአላት አከባበር ፣ የወልድያ መሰናዶና የወልድያ ዩንቨረስቲ ፣ ወልድያን ወደብ የሚያደርገው የባቡር መስመር የወጣቶች ማዕከል ፣ የሸህ ሙሃመድ ሁሴን አል አሙድ ኢንተርናሽናል ስታድየም እና ውብና ምቹ የሆኑት የአገልግሎት ሰጭ ተቋሞቿ ፣ የተረጋጋች እና ሰላም የሰፈነባት መሆኗ ፣ ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር እሴቶቿ ውበቷም መስህቦቿም ናቸው፡፡

በቅርበት ከገነተ ልኡል ፣ ከወልድያ ገብርኤል ፣ ከሲርንቃ እየሱስ ፣ ከዛምል ጊወርጊስ ፣ ከመርጦ ለማሪያም እና ከሰዋ ሜዳ ቂርቆስ እንዲሁም ከርቀት ከዜት በር ፣ ሰሌን ፣ ዳቦ ደፈር እና ባፌት ላይ ሆኖ ወልድያን መመልከት  ልዩና ማራኪነት ያለው መስህብ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

ተራሯቿ እሷ   ለማጀብ  ተብለው በልዩ ጥበብ የታጀቡ ጋርዶች መስለው እነሱም እድገቷን እንደ ሰው  ቁልቁል የሚመለከቱ ይመስላሉ፡፡

የየጁዎች መንገድ በቀኝም በግራ ፤

መአዛው ያውዳል ይላል ናትራ  ናትራ፤

አሽኩቲና አደሱ ጠራኝ ያሉባንጃ ፤

ናፈቀኝ ጎንደር በር የጉብል ማርገጃ፤

ሀገሬ ወልድያ ሰፈሬ ጨውሪጋ ፤

ከሚተላለፈው የደጋጎች መንጋ ፤

አጃቢዋ በዝቶ ቆሞ እንደ ወጋግራ፤

ደፈርጌ በስተቀኝ ገብሬል በስተግራ፤

አዳጎ ሰንብቸ እገባለሁ ሙጋድ፤

እናንተን አግኝቼ አያሻም ዘመድ፤

ገበያው ማክሰኞ ፍቅር መሸመቻ፤

ገዳይ ሴት ያለበት የወንዶች መሞቻ፤

ደግ ይበቅልበታል እንዳደይ አበባ፤

በወልድያ ራስጌ ከኩማንዳ ጠባ፤

የውበት ሰገነት የመውደድ ገበያ፤

ፍቅር ሞልቶ ይፈሳል በውቧ ወልድያ፤

ምንጭ­­—አብዱል ጀባር አህመድ

Share:

More Posts

የቱሪዝም ምንነትና መስህብ ሀብቶቻችን

የአለም ህዝቦችን በማቀራረብ የባህል ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ትልቅ የኢንዱስትሪ መስክ እየሆነ መምጣቱ ሁሉም እየመሰከረለት የመጣ መስክ ነው፡፡ ሰዎች ለተለያዩ አላማዎች ከቦታ

የቅርስ ምንነት እና ትርጉም

ይዘት መግቢያ ሐገራችን ኢትዮጲያ ካላት የተፈጥሮ ሐብት ቀደምት ህዝቦች የስራ ውጤት የሆኑት ቅርሶች ባለቤት መሆኗ የሚታዎቅ ነው፡፡ ለምሳሌ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም የበርካታ ሰው ሰራሽና

ባህል የማንነታችን  መገለጫ ነዉ!

ባህል፡- እንደ ማህበረሰብ ሳይንስ አጥኝዎች ትርጉም የሰዉ ልጅ ባህርይ ፣ እምነት ፣ ዝንባሌ ፣ እሴት እና አስተሳሰብ እንዲሁም በማህበራዊ ኑሯቸዉ ዉስጥ የሚማሩት ፣ የሚፈጥሩት እና

 ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች

የሰው ልጅ በህይት ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቱ መርካት አለበት፡፡ ከዚህ ዉጭ የሚፈፅማቸው ግን ደባል ወይም ትርፍ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህም ትርፍ ነገሮች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ወይም

Send Us A Message

Scroll to Top