ኪነ-ጥበብ የአንድህብረተሰብ እድገት የስልጣኔ ምጥቀት መግለጫ ነዉ፡፡ ኪነ-ጥበብ ማለት ሙዚቃና ዉዝዋዜ፤ ስእልና ቅርጻቅርጽ፤ ቲያትርና ስነ- ጽሁፍን አጠቃሎ የያዘ ነዉ፡፡ ከነዚህም የኪነ-ጥበብ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነዉን ስነ- ጽሁፍን በመዉሰድና የስነ- ጽሁፍ ምሽት ምን እደሆነ እንመለከታለን፡፡
ስነ-ጽሁፍ ምድን ነዉ?
ስነ- ጽሁፍ ስለሰዉ በሰዉ ለሰዉ የሚጻፍ የህይወት ገጽታዎችን አግዝፎ በማሳየት ሰዉ ራሱንና አካባቢዉን መለስ ብሎ በዉል ለማጤን የሚያስችል ጥበብ ነዉ፡፡ ይህንን ምጥበብ ለማሳደግና ለማስፋፋት የስነ-ጽሁፍ ምሽት አስፈላጊ ነዉ፡፡
የስነ– ጽሁፍ ምሽት ምንድን ነዉ ?
የስነ- ጽሁፍ ምሽት ማለት ከምሽቱ 11፡30 ጀምሮ የሚደረግ /የሚካሄድ/ የስነ-ጽሁፍ ስራዎች የሚቀርቡበት የመድረክ ዝግጅት ነዉ፡፡ይህም የአማተር ጽሀፍትን በማነቃቃትና ለስነ- ጽሁፍ እድገት ትልቁን ሚና ይጫዎታል ተብሎ የሚታሰበዉ አንዱ የስነ- ጽሁፍ ምሽትነዉ፡፡
የስነ– ጽሁፍ ምሽት አላማ
- በከተማ አስ/ሩ / የስነ-ጽሁፍ ምሽትን በአድስ መልክና በዘመናዊ አሰራር በመቀየር ባልተቆራረጠና በተከታታይ ፕሮግራሙን ለማካሄድ እድቻል፡፡
ማኅበረሰቡን እያዝናኑ በማስተማር የኪነ-ጥበብ እርካታዉን ለመጠበቅ፡፡ አማተር ጽሀፍትን ችሎታቸዉን እንዲያወጡና እንዲጠቀሙበት ፡፡
- የህብረተሰቡ የንባብና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች ን የመጻፍ ፍላጎት እዲጨምር፡፡
- የእዉቀት የልምድና የፍላጎት ፈጠራዎች እንዲጎለብቱ ለማድረግ፡፡
የስነ– ጽሁፍ ምሽት መቸ ይዘጋጃል?
ከስሙ እንደምንረዳዉ የስነ- ጽሁፍ ምሽት የሚዘጋጀዉ በምሽት ነዉ፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት በስራ፣ በትምህርት ፣ በሌላም ምክንያት የደከመን አዕምሮ እንዲዝናና ለማድረግ የተሻለ ጊዜ ምሽት በመሆኑ ነዉ፡፡
ስለዚህ የስነ-ጽሁፍ ምሽቱ ከ11፡30 በኋላ ባለዉ ጊዜ ቢሆንና እንደታዳሚ ፍላጎትና እንደዝግጅቱ እየተጠና በቋሚነት መድረክ እየተዘጋጀለት ሊቀርብ የሚችል ዝግጅት ነዉ፡
የስነ– ጽሁፍ ምሽትን እንዴት ዉብና ማራኪ ለማድረግ ይቻላል?
የስነ-ጽሁፍ ምሽትን ዉብና ማራኪ ለማድረግ ሶስት /3/ የዝግጅት ምእራፎች ያስፈልጋሉ፡፡
1ኛ- ቅድመ ትግበራ ዝግጅት
2ኛ- የትግበራ ዝግጅት
3ኛ- የማጠቃለያ ዝግጅት በማለት ማየት ይቻላል፡፡
ቅድመ ትግበራ ዝግጅት ማለት የምሽት ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት የሚደረጉ ዝግጅቶች ናቸዉ፡፡ እንዝህም የቅድመ ትግበራ ዝግጅቶ የምንላቸዉ፦
- የቅስቀሳ ዝግጅቱን የማስተዋወቅ ስራ
- የስነ- ጽሁፍ ስራዎችን መሰብሰብና መምረጥ/መገምገም
- የስነ-ጽሁፍ አዘጋጅ ኮሚቴን ማዋቀር
- ጥሪ የሚደረግላቸዉን አካላትመምረጥና ጥሪ ማስተላለፍ
- በስነ- ጽሁፍ የተደራጁ ማህበራትና ክበባትን ሌሎችንም አይቀሩም የሚባሉ ክፍሎችን በጥሪ ወረቀት መጥራት፡፡
በትግበራ ጊዜ የሚቀርቡ ዝግጅቶች
የትግበራ ዝግጅት ስንል የስነ- ጽሁፍ ምሽቱ በሚደረግበት እለት የሚከናወኑ ተግባራትን ሲሆን፡እነዚህም ተግባራት
- የምሽቱ አዘጋጅ ኮሚቴ የስራ ክፍፍል ማድረግ
- በእለቱ የሚቀርበ የተመረጡ ስራዎች/ጽሁፎች/ በተመረጡ የኮሚቴ አባል እድያዙ ማድረግ፡፡
ታዳሚን እያዝናና የሚያነቃቃ ተሰጥኦ ያለዉ ጥሩ የመድረክ መሪ ማዘጋጀት
- በተለያዩ የመቀስቀሻ ዘዴዎች የቅስቀሳ ስራ መስራት
- መድረኮችን ማዘጋጀትና ማስዋብ
- የታዳሚ ቦታ ማዘጋጀትና ቦታ ማስያዝ
- በተቻለ መጠን መድረኩን ማድመቅ
- በምሽት የሚቀርቡ የስነ- ጽሁፍ ስራዎችን በቅደም ተከተል ማቅረብ
- ስለ ምሽቱ ፕሮግራም የአስተያየት መሰብሰቢያ መጠይቅ መበተን የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
የማጠቃለያ ዝግጅት
ይህ ምእራፍ የስነ-ጽሁፍ ምሽቱ የሚጠናቀቅበትዝግጅት በመሆኑ ዝግጅቱ ከተጠናቀቀ በኋላ
- ስለ እለቱ ዝግጅት ከ 3 ላልበለጡ ሰዎች አስተያየት እንዲሰጥ መጋበዝና አስተያየቶችን በማስታዎሻ መያዝ
- የተበተነዉን የአስተያት የመጠይቅ ወረቀት ከታዳሚዉ መሰብሰብ
- የዝግጅት አቅራቢዎችንና በሙሉ ተሳታፊዎችን ማመስገን
- ከታዳሚ ስለዝግጅቱ የተሰጡ አስተያየቶችን ጊዜ ሳይሰጡ በጋራ ማየትና መገምገም ናቸዉ፡፡