Build Your Dream

 ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች

 የሰው ልጅ በህይት ለመኖር  መሰረታዊ ፍላጎቱ  መርካት አለበት፡፡ ከዚህ ዉጭ የሚፈፅማቸው ግን  ደባል  ወይም ትርፍ  ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህም ትርፍ ነገሮች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ወይም  ደባል  ሱሶች እንላቸዋለን::  

 የሰው ልጅ በህይት ለመኖር  መሰረታዊ ፍላጎቱ  መርካት አለበት፡፡ ከዚህ ዉጭ የሚፈፅማቸው ግን  ደባል  ወይም ትርፍ  ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህም ትርፍ ነገሮች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ወይም  ደባል  ሱሶች እንላቸዋለን::  

እነዚህ ድርጊቶች በአካል ፣ በሰነ-ልቦና ፣ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊ  ህይወታችን ዙሪያ አሉታዊ ተፅእኖ  ያሳድራሉ::

የሰው ልጅ እንደሚጎዱት እያወቀ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን ወይም ደባል ሱሶችን የሚጠቀም ፍጡር ነው፡፡ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶቹም የሚያሰከትሉት  ጉዳት አብዛኛውን ጊዜ በሴቶችና ህፃናት ላይ ቢሆንም  የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል  ላይ ችግር ሲፈጥሩ ይስተዋላል::

የተወሰኑትን ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እናሳና  በማን0ሳት ለምን እንደሚፈፀሙ  እና  በህብረተሰቡ  ላይ የሚፈጥሩት ስሜትና የሚያሳድሩትን ተፅእኖ እንዲሁም አጠቃላይ  ጉዳታቸውን በጋራ እንይ፡፡

  1. አልኮል መጠጥ ሱስ፡ አልኮል መጠጣት  ጊዜን ገንዘብን አካልን ይጎዳል፡፡ አብዛኛዎቹ ጠጭዎች  ከተሜዎች ቢሆኑም በገጠሩም ቁጥሩ ቀላል የማይባል የሰው ሃይል እየገባበት ነው፡፡ በገበያ ቀንና በልዩ ልዩ  ምክንያቶች ወደ ከተማ ሲገባ  ከትንንሽ እስከመካከለኛ የመጠጥ አይነቶችን ሲጋት የሚውለው ብዙ ነው፡፡

ለቤቱ ጨውና በርበሬ በማሟላት ፈንታ  ቋጠሮውን  ሽጦ  ለመሸታ የሚያውለውን  ቤቱ  ይቁጠረው፡፡ አልኮል የመጠጣት  ልምድ ያለው ስው ለለከፋ ፣ለዝሙት  በመጋለጥ በህይወቱ ላይ አደጋ  ያሰከትላል ፡፡

አዘውታሪ ጠጭዎች ለምን አዘውትረው እንደሚጠጡ ሲገልፁ  ለመዝናናት፣ ለጨዋታና ለመነቃቃት ነው ይላሉ፡፡ ሳይጠጡ ቢቀሩ ግን  ይነጫነጫሉ ፣ይደበራሉ  ቁጡም ይሆናሉ፡፡

የመጠጥ ወዳጅ የሆነ ሰው መደበኛ ተግባራትን ከማከናወን ይልቅ በራሰ የመተማመን ስሜት የሸሸው፤ በጤናውና በገንዘቡ የተቃወሰ በትንንሽ ጉዳዮች  ወደ ግጭትና ጠብ የሚገባ ወንጀል  ፈፃሚ ፣ ትዳሩን የሚጠላ ፣በአጠቃላይ በአካልና በመንፈስ  የተራቆተ  ይሆናል፡፡

2. የጫት ሱስ፡ጫት  የመቃም ታሪክ  እንደኛ ከተማ አስተዳደር ም ሆነ  እንደአገራችን  ረጅም  እድሜ   ያስቆጠረ  ልምድ ነው፡፡  የሚቅሙትም  ግለሰቦች በእድሜ ጠና ያሉ ሲሆኑ  የሚቅሙትም   ግለሰቦች ረግመውም ሆነ ፀልየው የሚሰምርላቸው ናቸው ተብሎ የሚታመንባቸው ነበሩ፡፡

አሁን ግን  ፆታና እድሜ  ሳይለይ የቃሚው  ቁጥር  እየናረ እና  ሱሰኛው እየበዛ  ነው፡፡ በፀሎት መሳሪያነቱ  የሚጠቀሙ ቢኖሩም እንዝናናበት የሚሉት  ደግሞ አያሌዎች ናቸው፡፡

ራሱን የቻለ  ጥናት የሚያስፈልገው ቢሆንም  የእለት  ገቢ ካላቸው የሌላቸው  ቃሚዎች  እንደሚበዙም መገመት ይቻላል፡፡  ጫት በውስጡ ከያዘው ንጥረ ነገር /ኒኮቲን/ የተነሳ ያሉበትን ዓለም አስረስቶ  ቅ¡ት  ውስጥ በመክተት ጊዜያዊ ደስታን  ፈጥሮ ያልተጨበጠ  ተስፋን ያሳቅፋል፡፡

ፈር  የሌለው ሃሳብ ይከስትና በሰፊው ያስመኛል፡፡ ሱሰኞች ጫትን ባጡት ጊዜ ከልክ ያለፈ ድብርት ይጫናቸዋል፡፡ብስጩና ቁጡ ይሆናሉ$

በጫት ጭንቀት ይነግስና ወደ ስርቆት ወንጀል ሊያስገባ ይችላል

  • ኑሮን ያናጋል
  • ራስን ያስጥላል  /ግዴለሽነት ይጎለብታል/
  • የገንዘብና የጊዜ ብክነት  ያስከትላል
  • የጤና መታወክና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ያስከትላል
  • ማህበራዊ  ቀውስን ያስከትላል
  • ምርታማነትን ይቀንሳል፤ ልማትን ያስተጓጉላል

  • ማህበራዊ  ህይወትን ያናጋል

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን  ችግሮች በምናይበት ጊዜ  የጫት ሱስ ጠብታ ጥቅም የለውም፡፡

Share:

More Posts

የቱሪዝም ምንነትና መስህብ ሀብቶቻችን

የአለም ህዝቦችን በማቀራረብ የባህል ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ትልቅ የኢንዱስትሪ መስክ እየሆነ መምጣቱ ሁሉም እየመሰከረለት የመጣ መስክ ነው፡፡ ሰዎች ለተለያዩ አላማዎች ከቦታ

የቅርስ ምንነት እና ትርጉም

ይዘት መግቢያ ሐገራችን ኢትዮጲያ ካላት የተፈጥሮ ሐብት ቀደምት ህዝቦች የስራ ውጤት የሆኑት ቅርሶች ባለቤት መሆኗ የሚታዎቅ ነው፡፡ ለምሳሌ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም የበርካታ ሰው ሰራሽና

ባህል የማንነታችን  መገለጫ ነዉ!

ባህል፡- እንደ ማህበረሰብ ሳይንስ አጥኝዎች ትርጉም የሰዉ ልጅ ባህርይ ፣ እምነት ፣ ዝንባሌ ፣ እሴት እና አስተሳሰብ እንዲሁም በማህበራዊ ኑሯቸዉ ዉስጥ የሚማሩት ፣ የሚፈጥሩት እና

ኪነ-ጥበብ ምንድን ነዉ?

ኪነ-ጥበብ የአንድህብረተሰብ እድገት የስልጣኔ ምጥቀት መግለጫ ነዉ፡፡ ኪነ-ጥበብ ማለት ሙዚቃና ዉዝዋዜ፤ ስእልና ቅርጻቅርጽ፤ ቲያትርና ስነ- ጽሁፍን አጠቃሎ የያዘ ነዉ፡፡ ከነዚህም የኪነ-ጥበብ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነዉን

Send Us A Message

Scroll to Top