ባህል፡- እንደ ማህበረሰብ ሳይንስ አጥኝዎች ትርጉም የሰዉ ልጅ ባህርይ ፣ እምነት ፣ ዝንባሌ ፣ እሴት እና አስተሳሰብ እንዲሁም በማህበራዊ ኑሯቸዉ ዉስጥ የሚማሩት ፣ የሚፈጥሩት እና የሚጋሩት የህይዎት ክፍል ሲሆን በሰዎች የኑሮ ሂደት ዉስጥ እለት ተእለት የሚንጸባረቅ እና የሚታይ ረቂቅ እና ግዙፍ ሃብት ነዉ፡፡
ሰዎች ቋንቋቸዉን እምነታዊ ክንዋኔያቸዉን ኪነ-ጥበባዊ እና ስነ ጥበብ ስራቸዉን፣ ቴክኖሎጂ፣ አለባበስ፣ የሰብል አመራረት እና አበሳሰል ልምድ እንዲሁም የሰዎች በህብረተሰብ ዉስጥ ያላቸዉ የፓለቲካና የኢኮኖሚ መስተጋብርን ሁሉ የሚያጠቃልል ነዉ፡፡ ባህልን ልዩ የሚያደርገዉ በርካታ ባህርያት አሉት፡፡
እነዚህም ተለዋዋጭ የሆኑ የሰዎች ባህርያትና የሚንቀሳቀሱና በማይንቀሳቀሱ ግኡዛን ምልክቶች ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ ሰዎች በቆይታ ጊዜያቸዉ የሚጋሩት፣ የሚማሩትና የሚለምዱት፣ ነዉ፡፡
የሚወርሱትና የሚያስተላልፉት እሴቶች ጭምር ነው
ከነዚህ ባህላዊ እሴቶቻችን መካከል ደግሞ ኪነ-ጥበብ አንዱ ነው
ኪነ-ጥበብ፡ ሰዉ በማህበር መኖር ከጀመረ አንሥቶ አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ በማህበራዊ መስተጋብሩ በኑሮኡደት ኪነ-ጥበብን የታሪኩ መተግበሪያና ከትቦ ማስቀሪያም ጭምር አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡
ኪነ-ጥበብ የሚለዉ ቃል ከስሙ እንደምንረዳዉ በዉስጡ ብዙ የጥበብ ዘርፎችን የያዘ ጥቅል የጥበብ ዘርፎች መጠሪያ ነዉ፡፡
ለምሳሌ በዉስጡ ስነ-ፅሁፍ፤ሙዚቃና ዉዝዋዜ፣ትያትር፣ፊልም፣ስዕልና ቅርፃቅርፅ የመሳሰሉትን የጥበብ ዘርፎች ያጠቃልላል፡፡
እነዚህ የጥበብ ዘርፎች ደግሞ ለአንድ ሃገር ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና፣ፓለቲካዊ እድገት መጠነ ሰፊ ድርሻ እንዳላቸዉ አለ አይባልም፡፡
የኪነ-ጥበብ ዋነኛ ጉዳይ ሰዉ/ ማህበረሰብ/ ነዉ፡፡ ፈጣሪዉም ተቀባዩም ነዉ፡፡ ይህ ከሆነ ዘንድ ዘርፉን ለማሳደግና ለመደገፍ ባለ ድርሻ የሚሆነዉም ህብረተሰቡ ነዉ፡፡
ኪነ-ጥበብ ለሁሉም ነገር በሁሉም ቦታ ተፈልጎ ወይም የግድ ሆኖ ሲከሰት ማስተዋል የተለመደ ክስተት ነዉ፡፡ የሰዉ ልጅ የህይወቱ ቅመም ፣ ዉበት እንዲሁም ለደስታ እና ሃዘኑ መተንፈሻዉ አድርጎም ተጠቅሞበታል፡፡
ቢያንስ የእያንዳንዱ ሰዉ ስብእና የሚገነባዉ ከወላጆቹና አብሯቸዉ ከሚኖር የማህበረሰቡ አባላት በሚነገረዉ አፋዊ፣ቃላዊ እና ድርጊታዊ ኪነ-ጥበባዊ ክንዋኔዎች ነዉ፡፡ለሰዉ ልጅ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ እድገት የኪነ-ጥበብ እጅ ያለበት ለመሆኑ አያጠራጥርም ፡፡
ከዚህ በተቃራኒው ከባህላችን ጋር ተቀላቅለው በበርካታው የህይወታችን ገጽታ ላይ ተጽእኗቸውን ያሳረፉ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችና አስተሳሰቦችም አሉን፡፡
ጎጅ አስተሳሰቦቹና ልማዳቹ የመበርከታቸውን ያህል የሚያሳድሩት ተፅእኖም በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ላይ ነው፡፡ በጠቅላላው ህብረተሰብ በቡድንና በተናጠል ብሎ ማስቀመጥ ይቻል እንደሆን እንጅ በዝርዝር ቢገለፅ አውሎ ያሳድራል፡፡
ይህ ማለት ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችና አስተሳሰቦች ሲፈፀሙ የሰለባው ክንድ የሚያርፍባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሴቶች፤ ህፃናት እንዲሁም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ከሚባሉት መካከል የተትረፈረፈ ድግስ፤ ደባል ሱስ፤ የሴት ልጅ ግርዛት፤እንጥል ማስቆረጥ፤ ግግ ማስፈልፈል፤ ባእድ አምልኮ የተንዛዛ የለቅሶ ስርዓት እና የበአላት ቀን መብዛት የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችንና አስተሳሰቦችን መተግበርም ሆነ ማስተግበር አገራችን የተያያዘችውን ሁለንተናዊ የእድገት ጉዞ በመጎተት በኩል የአንበሳውን ድርሻ ከያዙ እንቅፋቶች አንዱ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡
በመሆኑም የችግሩን አስከፊ ገፅታ የተረዳውና መጥፎውን የማስወገድ ብሎም መልካሙን ማዳበርና ባህል የእድገት ሚናውን እንዲጫወት ሃላፊነት ያለበት የስራ ሂደታችን በወልድያ ከተማ አስተዳደር በጉልህ ይስተዋላሉ ያላቸውን ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችና አስተሳሰቦች በመለየትና ጥቅምና ጉዳታቸውን ከፈፀሚና አስፈፃሚዎች ጋር በመወያየት ችግሩን መፍታት ይቻላል ብሎ ያምናል፡፡
እንደ ከተማ አስተዳደራችን ተጨባጭ ሁኔታ የሚስተዋሉት ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችና አስተሳሰቦች ስናይ የተትረፈረፈ ድግስ ደባል ሱስ ባእድ አምልኮ
የተንዛዛ የለቅሶ ስርአት ግግ ማስፈልፈልና እንጥል ማስቆረጥ አልፋልፎም ያለድሜ ጋብቻና ያላቻ ጋብቻ ይስተዋላሉ፣፣
እነዚህን ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችና አስተሳሰቦች ለመከላከል ብሎም ጨርሶ ለማስወገድ በመንግስትም ሆነ በህብረተሰቡ በኩል ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው