የአለም ህዝቦችን በማቀራረብ የባህል ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ትልቅ የኢንዱስትሪ መስክ እየሆነ መምጣቱ ሁሉም እየመሰከረለት የመጣ መስክ ነው፡፡
ሰዎች ለተለያዩ አላማዎች ከቦታ ቦታ እንደሚንቀሳቀሱ የሚታወቅ ቢሆንም ለመዝናናት፤ለሀይማኖታዊ ክብረ በአሎችና ለንግድ የሚያደርጉት እንቅስቃሴዎች ጎልተው የሚታዩ ናቸው፡፡
በዚህ ረገድ የሀገራችን ዜጎችም ሆነ ለሌላው ህዝብ ቱሪዝም የአለም ህዝቦችን በማቀራረብና በማስተዋወቅ የባህል ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል በማበርከትም ላይ ይገኛል፡፡
በግልም ሆነ በአገርህን እወቅ ክበባት በመደራጀት በተፈጥሮ፤ በታሪክ፤ በባህል ቅርሶችና በቱሪስት መስህቦች እምቅ ሃብት ያለችውን ኢትዩጵያን የመጎብኝት ልምድ እንዲያዳብሩና እንዲያዘወትሩ በጉብኝት ከሚያገኙት እርካታ/ደስታ ባሻገር ሃገራቸውን በውል እንዲያውቁና ሌሎችንም በማሳወቅ የአካባቢያችንን በጎ ገፅታ ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡
የሃገራችንን ቱሪዝም በማስፋፋት በኢትዩጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መካከል የበለጠ መቀራረብና መተዋወቅ ፤ ለጋራ እሴቶቻቸው በጋራ የሚሰሩበት እንዲሁም የህዝቦች ለህዝቦች መከባበርና ለአገራዊ ይሁንታ ብሄራዊ ስሜት መጎልበትና ለጋራ ብልፅግና አንድ ጠንካራ የኢኮኖሚ ማህበ ረሰብ የመገንባት
ቱሪዝም ከጉዞና ጉብኝት ጋር የተያያዘ አግልግሎት ሰጭ የኢንዱስትሪ ዘርፍ በመሆኑ ከመሠረተ ልማትና ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች ዕድገት ጋር በፍጥነት እየተስፋፋና እያደገ የመጣ ዘርፍ ነው፡፡
ቱሪዝም በሃገራችን እድሜው ገና ለጋ በመሆኑ የመሠረተ ልማት ችግሮቹና የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ችግሮች ጎልተው የሚታዩ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ቱሪዝም በአለም አቀፍ ደረጃ ገና በትንሽ እድሜው ላይ የሚገኝ ዘርፍ በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ ትርጉም አልተሰጠውም ይሁን እንጅ አብዛኛው የዓለም ህዝብና የቱሪዝም ሊቃውንት የሚስማሙበት የዓለም ቱሪዝም ድርጅቶችWTO/
ትርጓሜ
ቱሪዝም ሰዎች ከሚኖሩበት ከተለመደው አካባቢ ለመዝናናት ለጉብኝት ለዓምልኮ፣ ለኮንፈረንስ፣ ወዘተ የሚያደርጉት ጉዞ ሆኖ በሄዱበት አካባቢ ከአንድቀን ላላነሰ ከ1ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ቆይታ የሚያደርጉበት እንቅስቃሴ ነው፡፡››
ስለሆነም ተጓዡ በሄደበት ቦታ የሚያወጣው ወጭ በአካባቢው የሚሸፈን ከሆነ ተጓዥ ቱሪስት አይባልም፡፡
ቱሪዝም ለድህነት ቅነሳ የሚያደርገው አስተዋፅኦ
ለመሠረተ ልማት አውታሮች መዘርጋት ለገጠር ነዋሪች ከግብርና ውጭ /መንገድ በመምራት በቅሎ በማከራየትና ሌሎች የጉልበት ስራዎችን በመስራት/ የስራ መስክ በመፍጠር አማራጭ የገቢ ምንጭ በመሆን ያገለግላል፡፡ከተማዋ ገቢ ገምታገኝባቸው መካከል
የቱሪዝም አውታዊና አሉታዊ ተፅዕኖዎች
ማህበራዊ
- አካባቢያዊ ዕድገትን ያፋጥናል
- ማህበራዊ ዕድገትን ያጠናክራል
- የገጠርና የከተማ ትስስርና ዕድገትን ያፋጥናል
- ድህነትን ለመቀነስ ብሎም ለማስወገድ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ወ/ዘ/ተ
ባህላዊ
የተለያዩ የብሄረሰቦች ባህል፤ አለባበስ፤ አመጋገብ ሃይማኖትና ቋንቋ ባህላዊ የአደን መሳሪያዎችና መገልገያ ቁሳቁሶች ወ.ዘ.ተ ለመጠበቅና ጥገና ለማድረግ ፤ ለመንከባከብ ያስችላል
አካባቢያዊ
- አካባቢን ለመጠበቅና ለማስዋብ ይረዳል
- የተለያዩ ብርቅዩ ወፎች፣ አጥቢዎች የዱር እና የውሃ ውስጥ እንስሳትን ለመጠበቅ ያሥችላል
ታሪካዊና ሰው ሰራሸ መስህቦች
- ማካነ መቃብሮችና የቅርስ ጥናት ቦታዎችን ለመጠበቅ ያሥችላል፡፡
- ገዳማት አድባራትና መስጊዶች ለመንከበሰከብ፣ ለመጠበቅና ለመጠገን ያሥችላል፡፡
- ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ዋሻዎችን ለመጠበቅና ጥቅም ላይ ለማዋል ያስችላል፡፡
- ህ/ሰቡ በአካባቢያውና በማንነቱ እንዲኮራና የሃገር ፍቅር ስሜት እንዲያድርበት ያደርጋል፡፡
አሉታዊ ተፅዕኖ
- በትክክልና በጥንቃቄ ያልተመራ ቱሪዝም የሚከተሉትን ጉዳቶችን ያደርሳል፡፡
ኢኮኖሚያዊ
የውጭ ምንዛሬ ዕጦት ይፈጥራል /የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘት ይልቅ የውጭ ምንዛሬ እንዲወጣ ሊያደርግ ይችላል፡፡/
- የገንዘብ የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ያደርጋል
- የአካባቢው ህ/ሰብ በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት አጠቃቀም ረገድ የተዛባ/አነስተኛ/ መሆንን ይፈጥራል፡፡
ባህላዊና ማህበራዊ ተፅዕኖዎች
- ባህላዊ ቅርሶች የመበከልና የውድመት አደጋ ያስከትላል፡፡
- የህ/ሰቡን ባህል የመበረዝ አደጋ ያጋጥማል
- ጎጅ ያልሆኑትን ባህልና ወጎች የመጥላትና በመጤ ባህል እንዲተካ ያደርጋል፡፡
ወጥ የሆነ ዕደ ጥበባት፣ ኪነ ጥበባትና ስነ-ጥበባት እንዲጠፋ ያደርጋል፡፡
የተፈጥሮና አካባቢያዊ ተፅዕዎች
- የውሃ ብክለት ያስከትላል
- የአየር ብክለትን ያስከትላል
- የድምፅ ብክለትን ያስከትላል
- የእይታ ብክለትን ያስከትላል
- የደኖችና የዱር እንስሳት ውድመት ያስከትላል
ፓለቲካዊ ተፅዕኖዎች
- ለአገራችን ተስማሚ ያልሆነ ፓለቲካዊ ተፅዕኖ ሊያስከትል ይችላል
- ከእድገታችን ጋር ተመጣጣኝ ያልሆነ አስተሳሰብ ይፈጥራል፡፡