Build Your Dream

የሸህ ሙሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ ስታድየም ለከተማችን ይዟቸው የሚመጡ መልካም እድሎች እና ፈተናዎች

የሸህ ሙሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ የወልድያ ስታድየም ከእግር ኳስ መጫወቻነት ባለፈ በውስጡ የመዋኛ ገንዳ ፣ የመሮጫ ትራክ ፣ የቅርጫት ኳስ ኮርት ፣ ፊልድ ቴኒስ እና ሌላም የአትሌቲክስ ፋሲሊቲዎችን አሟልቶ የያዘ ሁለገብ ስታዲየም  ነው። ስታዲየሙ 25000 ሰዎችን የማስተናገድ አቅም አለው።

 14409932_1785897285025249_6559179289959227941_o

የወልድያ ስታዲየም ፕላን 2003

የስታዲየሙ ግንባታ በአምስት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ ታስቦ ግንባታው የተጀመረው በ2003 ዓ.ም ነበር። ግንባታው ከተጠናቀቀ ብኋላ ኢትዮጲያ አህጉራዊ ጨዋታዎችን ታዘጋጃለች የሚል አዲስ ብሩህ ተስፋ እነድንሰንቅ አስችሎናል።

በዚህ ወቅት ቱሪዝም በአለም አንዱና ትልቁ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለ የምጣኔ ሃብት ሴክተር ሲሆን አጠቃላይ የአለምን 10% GDP እና 1/10 የአለምን ሰራተኛ የመቅጠር እምቅ ሃይል አለው። ለዚህ የስታቲስቲክስ አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል ደግሞ አንዱ የስፖርት ቱሪዝም ነው። ምክኒያቱም ስፖርት የአለማችን ትልቁ ማህበራዊ ክስተት ነውና። ሆኖም በስፖርት እና በቱሪዝም መካከል ያለው ግኑኝነት ተመጋጋቢ በመሆኑ ፈጣን እምርታዊ ለውጥን

አሳይቷል። የነዚህ ሁለት ኢንዱስትሪዎች ጥምረትም ዛሬ ላይ የስፖርት ቱሪዝምን ፈጥሯል። በዚህም ምከኒያት ሴክተሩ ፈጣን እምርታዊ ለውጥን እንዲያሳይ አስችሎታል። የነዚህ ሁለት ኢንዱስትሪዎች ጥምረትም ዛሬ ላይ የስፖርት ቱሪዝምን ፈጥሯል።

 ማህበራዊ ፋይዳ

የስፖርት ቱሪዝም በአዘጋጁ ከተማ ማህበረሰብ ላይ ካለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በዘለለ የራሱ የሆነ ማህበራዊ  ፖለቲካዊ እና አካባቢያዊ ተፅእኖዎች ያሉት ሲሆን  የማህበረሰባችነን አካላዊ እና አዕምሯዊ ጤና እንዲጎለብት ያስችለናል። የህክምና ወጫችን እንዲቀንስ ይረዳናል። ከዚህ ባሻገር የስፓርት ቱሪዝም የህዝብ ለህዝብ ትስስራችን እንዲጠነክር ፣ ወንጀል እንዲቀንስ ፣ ፀረ ማህበራዊ ባህርያት እንዲወገዱ ያስችላል።

የሸህ ሙሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ ሁለገብ ስታድየም ለወልድያና አካባቢዋ ህብረተሰብ ትልቅ የመዝናኛ ማዕከል ሲሆን የማህበረሰቡን ኩራት እና የነቃ ተሳትፎ ያጎለብታል። ምክኒያቱም ስፖርት አወንታዊ ለውጥ ወይም እድገት እንዲያመጡ የሚያስችል እና በህብረተሰቡ መካከል መልካም መቀራረብ እንዲኖር የሚያስችል የማህበረሰባችን የለውጥ ነፀብራቅ ነውና።

ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ በማህበረሰባችን የሚስተዋሉ የወንጀል ድርጊቶች እና ፀረ ማህበራዊ ድርጊትና ባህሪን እንዲሁም ስፖርት የሃገራችን ህዝቦች የአንድነት መገለጫ እንዲሆን ያስችለናል። ይህ ማለት የተለያዩ ብሄር ብሄረስምሰቦች እና ህዝቦች ፣ ሃይማኖቶች ተቻችለው በሰላም አብረው የሚኖሩበት መድረክ ይሆናል ማለት ነው።

fb_img_1470222261136

በከተማችን እና በሌሎች ከተሞች ወይም በፕርሜርሊጉ በሚደረጉ ጨዋታዎች ምክኒያት የህዝብ ለህዝብ ግኑኝነታችን እንዲጠነክር ያደርጋል። ህብረተሰባችን ከጠርዘኝነት ፣ ከብሄርተኝነት ፣ ከጎጠኝነት አመለካከት እርቆ አንዱ አንዱን በቀና እይታ የሚያይበት መነፀር ይሆናል። በደጋፊዎች መካከል በሚኖረው ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ከተማችን የዚህ ግዙፍ ስታዲየም ባለቤት በመሆኗ ገፅታዋን በመላ ሃገሪቱ በማስተዋወቅ ባለሃብቶችን ፣ ጠንካራ እና ብቁ ሰራተኛን በመሳብ ፣ አምራቹን የገጠር ማህበረሰብ ምርቱን የሚሸጥበትን ሰፊ የገበያ እድል በመፍጠር ከከተማ እስከ ገጠር ፣ ከባለሃብት እስከ ጠንካራ እና ታታሪ ሰራተኛ ፣ ከስፖርተኛ እስከ ደጋፊ ፣ ከተመልካች እስከ ጋዜጠኛ ያለውን ሰፊውን ማህበረሰብ በማስተሳሰር የህዝብ ለህዝብ ግኑኝነታችነን የምናጠነክርበት መሳሪያ ነው።

 ምጣኔሃብታዊ ፋይዳ

የሸህ ሙሐመድ ሁሴን አል-አሙዲን ስታዲየም ትልቅ አገራዊ እና አህጉራዊ የስፖርት ውድድሮችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑ ተጨባጭ የምጣኔ ሃብት ጥቅሞችን ፣ የመሰረተ ልማት እድገትን የሚያፋጥን እና የከተማችነን ብሎም የሐገራችነን ገፅታ ለመገንባት የሚያስችለን የምጣኔ ሃብታችን የእድገት እርከን ነው።

13920154_1757998627815115_5669544372965931551_oየወልዲያ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች 2009

በመሆኑም ይህ አይነቱ ግዙፍ ኢንዱስትሪ የምጣኔ ሃብታችን  ምንጭ ከግብራና መር ኢኮኖሚ ይልቅ ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ ኢኮኖሚ እንዲኖረን ያስችላል። በዚህም ምክኒያት ከተማችን እድገቷ እንደ ሃረግ የምትመዘዝበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ይህ በእጃችን ላይ ያለውን ሰፊና ጥልቅ እድል በጥበብ እንጠቀምበት ዘንድ የከተማ አስተዳደራችን እንዲሁም የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን የሚያስተዳድሩ አካላት እራሳቸውን ከኪራይ ሰብሳብሳቢነት በማራቅ በቁርጠኝነት ሌሎችን በመታገል እና እራስን በእውቀት እና በብቁ አመራርነት በማስታጠቅ የከተማችነን የለውጥ ሽግግር ላይ ሁላችነም የራሳችነን አሻራ አኑረን በማለፍ ታሪክ የሚወቅሰው ሳይሆን ትውልድ ሁሌም የሚዘክረው ሰው ሆነን ማለፍ ይኖርብናል።

ምንም እንኳ እንዳደጉት ሃገራት የስፖርት ቱሪዝም በምጣኔ ሃብታችን ላይ ትልቅ ተፅእኖ መፍጠር አይችልም ብለን ብናስብ አሁን ያለውን የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎቻችነን ሁሉ የሚያሳድግ እና የሚደግፍ ፣ አዳዲስ እና ተጨማሪ የኢንቨስትመን እድሎችን የሚፈጥርልን መሆኑን ልናውቅ ግድ ይለናል።

 7af69804-4a8e-4f9a-8d83-ed3af7c17bb9

 አካባቢያዊ ፋይዳ

እንደሚታወቀው ሰው ሰራሽም ሆነ የተፈጥሮ ሃብትን የተላበሰ አካባቢ ለቱሪዝም እድገት አስፈላጊ ነው። ነገርግን ቱሪዝም እና አካባቢ ያላቸው ግኑኝነት ውስብስብ ነው። የሆኖሆኖ በአካባቢው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚያሳድሩ በርካታ ክስተቶችን አቅፎ ይዟል። አብዛሃኛዎቹ ስራዎችም ከአጠቃላይ የመሰረተ ልማት ግንባታ እና የቱሪዝም ፋሲሊቲዎች ማለትም መናፈሻ ፣ ሆቴሎች ፣ ሬስቶራንቶች ፣ ሎጅዎች ወዘተ ጋር የተያያዘ ነው። ከዚህ በተቃራኒ የስፖርት ቱሪዝም ለአካባቢያችን የተፈጥሮ ሃብት መልማት ጠቃሚ ተፅእኖዎች አሉት። ለምሳሌ፦ የተቀናጀ ስራ በመስራት ለአካባቢው የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ የአንበሳውን ድርሻ ይወጣል። እንዲሁም ስለ አካባቢያችን የተፈጥሮ ሃብት ግንዛቤ ለመፍጠር እንደ መሳሪያነት ያገለግለናል።

  • የስፖርት ማዘውተሪያውን የህዝብ እና ለህዝብ በማድረግ የአካባቢውን የተፈጥሮ ሃብት በወጉ እንዲጠበቁ እና እንዲለሙ ማድረግ ያስችላል።
  • ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የተራቆቱ ቦታዎች እንዲለሙና እንዲጠበቁ የማድረግ ስራ ለመስራት አመች ነው።

Share:

More Posts

የቱሪዝም ምንነትና መስህብ ሀብቶቻችን

የአለም ህዝቦችን በማቀራረብ የባህል ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ትልቅ የኢንዱስትሪ መስክ እየሆነ መምጣቱ ሁሉም እየመሰከረለት የመጣ መስክ ነው፡፡ ሰዎች ለተለያዩ አላማዎች ከቦታ

የቅርስ ምንነት እና ትርጉም

ይዘት መግቢያ ሐገራችን ኢትዮጲያ ካላት የተፈጥሮ ሐብት ቀደምት ህዝቦች የስራ ውጤት የሆኑት ቅርሶች ባለቤት መሆኗ የሚታዎቅ ነው፡፡ ለምሳሌ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም የበርካታ ሰው ሰራሽና

ባህል የማንነታችን  መገለጫ ነዉ!

ባህል፡- እንደ ማህበረሰብ ሳይንስ አጥኝዎች ትርጉም የሰዉ ልጅ ባህርይ ፣ እምነት ፣ ዝንባሌ ፣ እሴት እና አስተሳሰብ እንዲሁም በማህበራዊ ኑሯቸዉ ዉስጥ የሚማሩት ፣ የሚፈጥሩት እና

 ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች

የሰው ልጅ በህይት ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቱ መርካት አለበት፡፡ ከዚህ ዉጭ የሚፈፅማቸው ግን ደባል ወይም ትርፍ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህም ትርፍ ነገሮች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ወይም

Send Us A Message

Scroll to Top