Build Your Dream

​ኑ ወልድያን እናሰተዋውቃችሁ

በ18ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው አጋማሽ ጀምሮ መሳፍንቶች ግዛታቸውን ለማስፋፋት በሚያደርጉት ፍልሚያ ከጎንደር ባሻገር የጁን ለማስገበር ግስጋሴያቸውን በሁሉም አቅጣጫ አፋጠኑት በመጨረሻም አላማቸው ተሳክቶላቸው ጎንደርንና የጁን አጣምሮ መግዛት ቻሉ፡፡

በ18ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው አጋማሽ ጀምሮ መሳፍንቶች ግዛታቸውን ለማስፋፋት በሚያደርጉት ፍልሚያ ከጎንደር ባሻገር የጁን ለማስገበር ግስጋሴያቸውን በሁሉም አቅጣጫ አፋጠኑት በመጨረሻም አላማቸው ተሳክቶላቸው ጎንደርንና የጁን አጣምሮ መግዛት ቻሉ፡፡

በ1777 በወቅቱም መናገሻን /ከተማን/ለመቆርቆር ተራሮችን/ከፍተኛ ቦታዎችን/ ተገን ማድረግና ራስን ከጥላት ለመጠበቅ የዶሮ እንቅልፍ መተኛት ግድ የሚል ነበር፡፡ 

የሀር ሀረጋቸው ከደቡባዊቷ የአረብ ሀገር የመን እንደሆነ የሚነገርላቸው ታላቁ እራስ አሊ ጎንደርንና የጁን አጣምረው የሚያስተዳድሩበት መናገሻ የሚሆን ለወታደራዊ ስትራቴጅክ የሆነ ቦታ ያስፈልጋቸው ነበር፡፡

በዚህም የጥንቷን ገነቴን የአሁኗን ወልደያን ከመሀል አግርገው ከተገተሩት የጉባርጃና የገብርኤል ተራሮች የሚስተካከል ሌላ አማራጭ አልነበረም፡፡

ጉባርጃና ገብርኤል ስር የተፈጠረችው ገነቴ የታላቁ ራስ አሊ ከገነቡበት የገብርኤል ተራራ አናት ሆነው ቁልቁል ሲመለከቱ በጊዜው ጥቅጥቅ ጫቃ እንደነበረችና በውስጧም የተለዩ አራዊት ይኖሩባት እንደነበር የሚነገርላት ገነቴ ላይ የአሁኑ ማክሰኞ ገበያ አካባቢ ነጭ ነገር ታያቸው በጊዜውም አሽከሮቻቸውን ምንነቱን እንዲያረጋግጡ ላኳቸው፡፡

አሽከሮቹ ሲመለሱም ነገሩ አንዲት ሴት ወልዳ አጥባ ያሰጣችው ልብስ መሆኑ ተነገራቸው፡፡ ንጉሱም አንዲት ሴት “ወልዳ” የሚለውን ሲሰሙ ቃሉን አደነቁ፡፡

ይህ ቃል ውሎ አድሮ አካባቢያዊ ዘዬ እየተጨመረበት “ወልዲያ” ወደሚል ቃል ተቀየረና የአካባቢው መጠሪያ እንደሆነ  የታሪክ ተመራማሪዎች ይነገራሉ፡፡ በሌላ በኩል ወልዲያ የሚለው ቃል የኦሮምኛ ቃል እንደሆነና ትርጉሙም “መገናኛ” ማለት እንደሆነ ይነገራል፡፡

ይህም ኦሮሞዎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በተሰደዱበት ጊዜ ለአካባቢው መጠሪያ ያወጡት ስያሜ እንደሆነም ይነገራል፡፡ 

ስለወልደያ አመሰራረት ለመንደርደሪያ የይህን አልንጅ የዚህ ጽሁፍ ዋና አላማ የነራስ አሊ ቤተ-መንግስት ከነበረበት የገብርኤል ተራራ ስር በስተሰሜን ምስራቅ በኩል የሚገኘውንና እጅግ ጥንታዊ እንደሆነ የሚነገርለት ባሁኑ ትውልድ ግን እንግዳና በውል የማይታወቅ ጥንታዊውን የምስራቀ ጽሀይ የማመጫ ተ/ሃይማኖትና ክርስቶስ ሰምራ አንድነት ገዳምን ለማስተዋወቅ ነው፡፡

የምስራቀ ጽሀይ የማመጫ ተ/ሃይማኖትና ክርስቶስ ሰምራ አንድነት ገዳም በድንቅ የቅርስ መስህብ ሀብቶች ባለቤትነት ከሚታወቀው የሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ አስተዳደር አደንጉር ገብርኤል ቀበሌ ድጎ እየሱስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትንሽ አለፍ ብሎ የሚገኝ ሲሆን ስለገዳሙ ታሪክ ትክክለኛና የተጻፈ ታሪክ ማግኘት ባይቻልም ከክርስቶስ ልደት በፊት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን እንደተመሰረተ አንዳንድ የገዳሙ አባቶች የተለያዩ ታሪኮችን በማጣቀስ ይናገራሉ፡፡ 

ገዳሙ ከወልዲያ ከተማ በመቀሌ መስመር ከ10 ደቂቃ የመኪና ጉዞ ቡኋላ ሽንቁሩን አለፍ ብሎ በስተግራ በኩል ከ1 ስዓት የዕግር ጉዞ ቡኋላ የሚገኝ ሲሆን ገዳሙ ስያሜውን ያገኘው አባ ሚጫ የሚባሉ አባት ይኖሩበት ስለነበር ከዚህ በመነሳት የአካባቢው ህ/ሰብ ማመጫ እንዳሉት አባቶች ይናገራሉ፡፡

አጠቃላይ የገዳሙ ይዞታ ከ5-6 ሄክታር የሚደርስ ሲሆን  ገዳሙ ካለው የተፈጥሮ መስህቦች መካከል በፈዋሽነታቸው አባቶች የሚመሰክሩላቸው 8 ጸበሎች ይገኛሉ፡፡ ይህም በርካታ ጸበሎችን በአንድቦታ ማግኘት ለሚፈልጉ ገዳሙን ተመራጭ ያደርገዋ፡፡

የማመጫ ገዳም እራስጌውን የገብርኤልን ተራራ ተንተርሶ በግርጌው ደግሞ የአላውሃ ወንዝን በማድረጉ የገዳሙ የተፈጥሮ ደንና በገዳሙ መነኮሳት የለማው አትክልትና ፍራፍሬ በገዳሙ ዙሪያ ካሉት ውብ የመልክአ ምድር አቀማመጥ ጋር ተደማምሮ አካባቢውን የምድር ገነት ያስመስሉታል፡፡

ያት ሁሉ በአካባቢው ተፈጥሮ አይናቸው ይማረካል፡፡ ታመው የሄዱ የሄዱ በጸበሎቹ ከደዌያቸው ተፈውሰው ቦታውን የጎበኙት አእምሯቸው ታድሶ እንደሚመለሱ ይመሰክራሉ፡፡ 

 ይሁንና በእጅ የያዙት ወርቅ እንዲሉ የወልዲያና አካባቢው ህ/ሰብ ወደ ገዳሙ አዘውትረው ሲሴዱና ሲጎበኙ አሊያም ሲጸበሉ አይታዩም እንዲያውም በርካቶች ገዳሙ ስለ መኖሩ በውል አያውቁም፡፡

ነገርግን በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ለአካባቢው የቅርብ ሩቅ የሆነውን የማመጫ ገዳምን የሚጎበኙና ገዳሙን የሚረዱ ምእመናን እንዳሉ የገዳሙ አባቶች ይናገራሉ፡፡

ለመሆኑ ገዳሙ ከወልዲያ በቅርብ እርቀት የሚገኝ ሆኖ ሳለ ለብዙዎች መሰወሩ ለምን ይሆን የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም፡፡ ይሀን አስመልክቶ የገዳሙ አባቶች እንደሚሉት ከ15ኛው ክ/ዘመን የግራኝ አህመድ ወረራ ጀምሮ አባቶች ገዳሙ እንዲደበቅና እንዳይታወቅ ያደርጉ እንደነበር ይናገራሉ፡፡

ምክንያቱም በወቅቱ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት በወረራው በመቃጠላቸው ገዳሙና የገዳሙ ይዞታ ከጥቃቱ ለመታደግ በሚል ነበር፡፡ ይህን ገዳሙን እስካሁን በጥቂቶች እንጂ በሰፊው የህ/ሰብ ክፍል እንዳይታወቅ የራሱ ተጽእኖ እንዳሳደረ ይነገራል፡፡ 

በገዳሙ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ከ30 በላይ ወንድና ሴት መነኮሳት የሚኖሩ ሲሆን የሚተዳደሩትም በገዳሙ ያለሙትን የተለያዩ የአትክልት ፍራፍሬዎች በመሸጥና እርሻ በማረስ ይተዳደራሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በተለያየ የእንስሳት እርባታ ኑሯቸውን ይደጉማሉ፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ በገዳሙ ግርጌ የሚያልፈው የአላውሃ ወንዝ ገዳሙን እየተፈታተነው ይገኛል፡፡ ይህም የእርሻ መሬታቸውን ጠራጎ እየወሰደ መነኮሳቶቹ ለልመና እጃቸውን እንዲዘረጉ እያስገደዳቸው ይገኛል፡፡

ወንዙ ሃይ የሚለው አካል ካላገኘ በገዳሙ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከዚህም ሊከፋ ይችላል፡፡ 

ወደገዳሙ ለጉብኝት ሲሄዱ አስታውሰው ሊጎበኟቸው የሚገቡ መስህቦች፡- 

ሌሎች አንዳንድ ገዳማት ወንዶችን ብቻ የሚያስተናግዲ ሲሆን የማመጫ ገዳም ግን ሁለቱንም ጾታ በቦታና በአኗኗር ለይቶ በማስተናገድ ልዩ ያደርገዋል፡፡

የገዳሙ ቤተመቅደስ ዋሻ የውስጥ ይዞታ ሰውሰራሽ ወይስ ተፈጥሯዊ የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ አለመኖሩና ጣራው የሻማ እንባ መስሎ የተንጠለጠለና ሲነኩት ግን እጅግ ጠንካራ የሆነ መሆኑና ምንም ዓይነት የእጅ ጥበብ አሻራ የሚያመላክት የሌለው መሆኑ

ዋሻውን በግራና በቀኝ አቅፈው የያዙት ዋርካዎች አፈጣጠራቸው /አበቃቀላቸው/ ግርምት የሚያጭር መሆኑ

የገዳሙ ዋሻ መግቢያ እንጂ መድረሻው የማይታወቅ መሆኑ

የገዳሙ መነኮሳት በአንድወቅት ቸግሯቸው በርሃብ አንገታቸውን ደፍተው በነበረበት ወቅት በወንዙ ሄዶ 52 ብር በጥርሶ ይዞ በመምጣት ለገዳሙ መጋቢ በመስጠት መነኮሳቶቹ የሚበላ ነገር በመግዛት ሂወታቸውን እዲያቆዩ ያደርጋቸው ችሎ የሚባለው ውሻቸው በአካል መኖሩ


በአጠቃላይ ስለ ማመጫ ገዳም የሚባሉትና የሖኑት ነገሮች በሙሉ ቢጻፍ እንኳ ይች ወረቀት መጽኃፍ ላይበቃው ይችላል፡፡ ማየት ማመን ነው እርሰስዎም ሄደው ይጎብኙ ከጠበቁት በላይ ይደመሙበታል፡፡

Share:

More Posts

የቱሪዝም ምንነትና መስህብ ሀብቶቻችን

የአለም ህዝቦችን በማቀራረብ የባህል ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ትልቅ የኢንዱስትሪ መስክ እየሆነ መምጣቱ ሁሉም እየመሰከረለት የመጣ መስክ ነው፡፡ ሰዎች ለተለያዩ አላማዎች ከቦታ

የቅርስ ምንነት እና ትርጉም

ይዘት መግቢያ ሐገራችን ኢትዮጲያ ካላት የተፈጥሮ ሐብት ቀደምት ህዝቦች የስራ ውጤት የሆኑት ቅርሶች ባለቤት መሆኗ የሚታዎቅ ነው፡፡ ለምሳሌ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም የበርካታ ሰው ሰራሽና

ባህል የማንነታችን  መገለጫ ነዉ!

ባህል፡- እንደ ማህበረሰብ ሳይንስ አጥኝዎች ትርጉም የሰዉ ልጅ ባህርይ ፣ እምነት ፣ ዝንባሌ ፣ እሴት እና አስተሳሰብ እንዲሁም በማህበራዊ ኑሯቸዉ ዉስጥ የሚማሩት ፣ የሚፈጥሩት እና

 ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች

የሰው ልጅ በህይት ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቱ መርካት አለበት፡፡ ከዚህ ዉጭ የሚፈፅማቸው ግን ደባል ወይም ትርፍ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህም ትርፍ ነገሮች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ወይም

Send Us A Message

Scroll to Top