Build Your Dream

​ስለቅርሶቻችን ምን ያህል  ያውቃሉ

ቅርስ ስንል በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ በክልልና በወረዳ እንዲሁም በሰፈር  ደረጃ  የሚታወቁና መለያ የሆኑ በዚያ አካባቢ ሚኖር  ህዝብ የታሪክ፣ የማንነትና የእውቀት  አሻራ  ያረፈባቸው ሁሉ ሚያጠቃልል ነው፡፡

ስለቅርስ በምናወራበት ጊዜ ሁሉም ስው የሚያወራው በአለም አቀፍ ደረጃ ወይም በሀገር አቀፍ ደረጃ ስለሚታወቅ ቅርሶች ሊሆን ይችላል፡፡

ነገር ግን ቅርሶች ስንል በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ በክልልና በወረዳ እንዲሁም በሰፈር  ደረጃ  የሚታወቁና መለያ የሆኑ በዚያ አካባቢ ሚኖር  ህዝብ የታሪክ፣ የማንነትና የእውቀት  አሻራ  ያረፈባቸው ሁሉ ሚያጠቃልል ነው፡፡

ስለዚህ ቅርስ የአንድ ህ/ሰብ አካባቢ የስልጣኔ ደረጃ የእውቀት ደረጃ እምነት ያሳለፏቸውን የታሪክ አጋጣሚ በበጎም ሆነ በመጥፎ ወ.ዘ.ተ የሚወክል ነው፡፡

 በከተማ አስ/ችን የሚገኝ የተለያዩ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ቅርሶች በመጠበቅና በመንከባከብ ለተለኪው ትውልድ ሚተላለፍ ከአሁኑ ትውልድ ይጠበቃል፡፡

 ይህንን ሃላፊነት ለመወጣት በከ/አስ/ችን  የሚገኙ ቅርሶችን  ዓይነት ብዛት ስርጭት በምን ሁኔታ  እንደሚገኙ ማወቅና መከታተል ያስፈልጋል፡፡

 ቅርስ ምንድ ነው

 ቅርስ የሚለው ቃል በፅነስ ደረጃ ሃሳብ ደረጃ በህ/ሰቡ ዘንድ ሆነ በሳይንስ መንገድ ከጠባብ ግንዛቤ በመነሳት ከግዜ ወደ ግዜ እየዳበረና እየሰፋ ሄዷል፡፡ የቅርስ ቃል የራሱ በሆነ አግባብና  ትርጓሜ  ከጥንተ ጀምሮ በህ/ሰቡ ይታወቃል፡፡

አንዳንድ ሰዎች መሰረታዊ የሆኑ ንብረቶች በከባድ ድካምና ልፋት የተገኙ መሆናቸውን ለመግለጽ ሲፈልጉ አሁን ገና ቅርስ ያዝኩኝ  ለፍቸ ያፈራሁት ቅርስ ነው፡፡ የመሳሰሉ አባባሎችን በመጠቀም ይገልፃሉ፡፡  

በሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስለ ቅርስ የተሰጠውን  ትርጉም በሚመለከት ስለቅርስ ምንነት አጠባበቅ በተከታታይ በወጡት  አዋጆች የተገለፀውን ለአብነት  መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡

በመጀመሪያ ስለ ጥንታዊ ቅርሶች ትርጉም የወጣው አዋጅ ቁጥር 229/1958 ጥንታዊ ቅርስ ማለት ከ1850 በፊት የተሰራ ማንኛውም  ዓይነት  ሰው ሰራሽ ስራ ወይም እቃ ነው፡፡ ተብሎ ሲገለፅ፡፡

 አዋጅ ቁጥር 36/1982 ደግሞ ቅርስ ማለት በኢትዮጵያ ቅድመ ታሪክና የታሪክ ዘመን በስነ ጥበብ፣ በሳይንስ በባህል ወይም በታሪካዊ ይዘታቸው  ከፍተኛ ተፈላጊነትና ዋጋ ያላቸው በማለት  ትርጉም ሲሰጥ አሁን ስራ ላይ ባለው ስለቅርስ ጥናትና አጠባበቅ  አዋጅ ቁጥር 209/1992 በአንቀፅ ¾ ላይ ቅርስ ማለት በቅድመ ታሪክና ታሪክ ዘመን የሰው ልጅ የፈጠራና የሥራ  እንቅስቃሴ ውጤት የሆነ የተፈጥሮ የለውጥ ሂደትን የሚገልፅና  የሚመሰክር በሳይንስ በታሪክ በባህል በስነ  ጥበብና በእደ ጥበብ ይዞታ ከፍተኛ ተፈላጊነትና ዋጋ ያለው ማንኛውም ግዙፍነት ያለውና ግዙፍነት የሌለው ነገር ነው፡፡ በማለት ይገለዋል፡፡

በሶስቱም አዋጆች ላይ የተሰጡት  ትርጓዎች ሲጠኑ መጠነኛ ልዩነት ከመኖራቸው በስተቀር   እርስ  በርስ የሚቃረኑ አይደሉም ይልቁንስ  ያልተካተቱትን እየጨመሩ በመምጣት በፅንስ በሃሳብ ደረጃ እየሰፋ መሄዳቸውን ይገልፃሉ፡፡ 

ማንኛውም የሰው ልጅ የፈጠራና የሥራ ውጤት የሆነውንና  የተፈጥሮ ገፅ በረከት ውጤቶችን በሙሉ ቅርስ ናቸው ብሎ ማጠቃለል  አስቸጋሪና አግባብነት የሌለው በመሆኑ ይህንን ውዝግብ ለማስወገድ  እንድቻል፡፡ አንድን ነገር ቅርስ  ሊያሰኙ የሚያስችሉ ነጥቦች/መስፈርቶች ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው፡፡ 

እነሱም፡-  

1ኛ  ታሪክንና ባህልን ለህ/ሰቡ በማስተማር ያለው ጠቀሜታ ሰፊና ከፍተኛ ከሆነ

2ኛ  በስነ ጥበባዊ ይዘቱ በአሰራር ጥረቱና ውበቱ ድንቅ ከሆነ

3ኛ የተሰራበት ንጥረ ነገር በጣም ውድና የማይገኝ ከሆነ 

4ኛ ለሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ያለው ጠቀሜታ የጎላ  ከሆነ 

5ኛ በእድሜ ጥንታዊ መሆን

6ኛ በግለ ወጥነቱና በናሙናነቱ እንዲሁም

7ኛ የተፈጥሮ ውበት ካለው/ድንቅ በሆነ የተፈጥሮ ሃብትነቱ/ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ 

የቅርስ ዓይነት

ቅርስ፡-  ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ

ሰው ሰራሽ፣-  ግዙፍነት ያለው  ግዙፍ የሌለው

ግዙፍነት ያለው፡- የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ  

የተፈጥሮ፡- ግዙፍነት ያለውና  ግዙፍነት የሌለው 

ግዙፍነት የሌለው፡-   የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ  

 የቅርስ ጥቅም

 የአንድ አገር ህዝብ መታወቂያና የክብሩ መገለጫ ሆኖ ያገለግላል

 የአንድ አገር ህዝን የማንነት መገለጫና የታሪክ ተጨባጭ መስረጃ በመሆን ከየት በመነሳት ከዚህ እንዲዳረስና የወደፊት የጉዞ ዘቅጣጫ ምን መሆን እንዳለበት በመጠቆም ያግዛል

 የቀደምት ሰዎችን አኗኗር ተግባር  እምነትና የእውቀት ደረጃ  ለመረዳት ይጠቅማል

 የተፈጥሮ  ክስተትን የሰው ልጅ አፈጣጠርን ማህበረራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገቱን ለማወቅ የጥናትና ምርምር መረጃ ምንጭ በመሆን ያገልግላል፡፡ ተተኪው ትውልድ ያለፈውን ትውልድ የፈጠራ ውጤት መነሻ በማድረግ ከዘመኑ ጥበብ ጋር በማዛመድ ይበልጥ በማሻሻል የፈጠራን ችሎታ ለማዳበር ይረዳል

 ቅርስ በህዝቦች ባህል  ግንኙነቶችና ልውውጦች የዳበረ  በመሆኑ ለህዝቦች አንድነት መሠረት በመሆን ለጋራ ዕድገት የሚዳረገውን ጥረት ያግዛል

 የህዝብን ብሄራዊ ስሜትና የሃገር ፍቅርን በማጎልበት ርስበርሱ  እዲተዋወቅ ልህልህንና ልምድን  እንዲለዋወጥና ይበልጥ እንዲቀራረብ ያደርጋል

 በአለው አለም አቀፋዊ ባህሉም ህዝቦችን ስሜትና ቀልብ በመሳብ  ለጉብኝት ከቦታ ወደ ቦታ ዝውውር እንዲሁም ተፅዕኖ ስለማሳድር በዓለም ላይ ሰላም እንዲሰፋን ምክንያት  ይሆናል፡፡

የህዝቦችን የኗኗር ዘይቤ በማንፀባረቅ የእኔ የሚል መለያ ለአካባቢው በማስገኘት ህ/ሰቡ ስለ አካባቢው ስለሃገሩ ስለማንነቱ የበለጠ እንዲያውቅና በራሱ መተማመንን እንዲያጎለብት በማድረገወ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

ቅርሶች ለመጎብኝትና በቅርሶች ላይ ጥናትና ምርምር  ለማካሄድ ከሚመጡ ቱሪስቶች በተለያዩ መልኩ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ በመሆን ለሃገር ኢኖሚ እድገት ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡

 ተተኪው ትውልድ ስለአለፈው ህ/ሰብ ይበልጥ እንዲያውቅ ግልፅ በሆነ መንገድ ለማስረዳት እንደማስተማሪያ  ሆነ ያገለግላል፡

Share:

More Posts

የቱሪዝም ምንነትና መስህብ ሀብቶቻችን

የአለም ህዝቦችን በማቀራረብ የባህል ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ትልቅ የኢንዱስትሪ መስክ እየሆነ መምጣቱ ሁሉም እየመሰከረለት የመጣ መስክ ነው፡፡ ሰዎች ለተለያዩ አላማዎች ከቦታ

የቅርስ ምንነት እና ትርጉም

ይዘት መግቢያ ሐገራችን ኢትዮጲያ ካላት የተፈጥሮ ሐብት ቀደምት ህዝቦች የስራ ውጤት የሆኑት ቅርሶች ባለቤት መሆኗ የሚታዎቅ ነው፡፡ ለምሳሌ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም የበርካታ ሰው ሰራሽና

ባህል የማንነታችን  መገለጫ ነዉ!

ባህል፡- እንደ ማህበረሰብ ሳይንስ አጥኝዎች ትርጉም የሰዉ ልጅ ባህርይ ፣ እምነት ፣ ዝንባሌ ፣ እሴት እና አስተሳሰብ እንዲሁም በማህበራዊ ኑሯቸዉ ዉስጥ የሚማሩት ፣ የሚፈጥሩት እና

 ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች

የሰው ልጅ በህይት ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቱ መርካት አለበት፡፡ ከዚህ ዉጭ የሚፈፅማቸው ግን ደባል ወይም ትርፍ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህም ትርፍ ነገሮች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ወይም

Send Us A Message

Scroll to Top